Testimonials

“ቆንጂት ገና በህጻንነቷ በጣም ወንድ ለመሆን ትፈልግ ነበር። ቀሚስ ሳለብሳት በፍጹም አትወድም፣ ያለሱሪ አታልብሱኝ ትል ነበር። ያኔ ገና ነው የጀግና አያቶቿ ደም በውስጧ እንዳደረ የገባኝ። እንደናት ሳልቀብራት መሞቷ ቢያንገበግበኝም የኔ ልጅ ታሪክ ሰርታ ማለፏ ግን ሁሌም ለኔ ኩራት ነች።” (እናቷ ሸዋሉል በቀለ)

“በጌምድር በለሳ የሚባል ቦታ ላይ ነበር ከኔ ጋር የተገናኘነው። እሷ ከአሲምባ ትግራይ በኤርትራና ሱዳን በኩል ዞራ ስንትና ስንት ቀናት የሚፈጅ የእግር መንገድ ተቋቁማ ነበር በጌምድር የገባችው። ጥንካሬዋ እንኳን በምቾት የኖረ የከተማ ሰው ልትመስል ቀርቶ እኛንም የምታስንቅ ታጋይ ጓዳችን ነበረች። ሁሌም ሳስበው ይደንቀኝ ነበር።ለብዙ ጓዶቻችን የመንፈስ ጽናት የሚሆነው የሷ ቆራጥነትና ህይወቷን ለዚህ ትግል መስጠት ነበር። አብረን ባሳለፍናቸው የትግል አመታት አንድም ቀን ስታማርር ሰምቻት አላውቅም። ደግነቷ ለከት የለውም፣ እጅግ ተጫዋች ነበረች። ትርሲት አስቀየመችኝ የሚል አንድ ሰው አይገኝም። በቁጣና በንዴት የመጣን ሰው ሁሉ የማብረድ ከፍተኛ ተሰጥኦ ነበራት። የድርጅት ዘርፍ ላይ ነበር በጣም የምትሰራው። የአካባቢውን ህዝብ እየሰበሰበች ታስተምራለች። ሲታመሙ አብራ አስታማ፣ ሲያዝኑ አዝና፤ ህዝቡ እንደ አይን ብሌኑ ነበር የሚያያት።”  (ፋሲካ በለጠ-የኢህአፓ ከፍተኛ አመራር)

አቶ እያሱ አለማየሁ (በብእር ስም፡ ባቢሌ ቶላ)፣ የኢህአፓ መስራችና ከፍተኛ አመራር ከትርሲት ጋር በቅርበት ይታገል በነበረበት የትግል ዘመን የህይወት ታሪኳን በመጽሀፍ እንድትጽፈው ይወተውታት እንደነበረና በመጨረሻም በከፊል ተሳክቶለት በቀይ ሽብር ወቅት ያሳለፈችውን ህይወት በወረቀት ላይ በመጻፍ የሰጠችው እንደሆነ ተናግሯል። ይህንን “Surviving the Red Terror” የተሰኘውን ጽሁፏን ለንባብ ሲያበቃው በመግቢያው ላይ ስለ ትርሲት እንዲህ ሲል የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል።  የባቢሌ ቶላ ምስክርነት

Mr. Eyasu Alemayehu (aka Babile Tola), founder and executive leadership of EPRP, had been trying to persuade her to write her life story during their time of struggle. She wrote a partial story of her life specifically focusing on a period of time when the struggle was at its peak. This book titled ‘Surviving the red terror’ was published later by him. In the book, he wrote the following intro and testimonial.               Testimonial of Babile Tola